Fana: At a Speed of Life!

ከ250 በላይ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛው የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ከ250 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ ተገለጸ፡፡

13ኛውን የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት አስመልክቶ ዛሬ በምክር ቤቱ መግለጫ ተሰጥቷል።

በመግለጫው እንደተገለጸው÷ የንግድ ትርዒቱ ከሚያዚያ 19 እስከ 23 ቀን 2015 ዓ.ም “የኢትዮጵያን ይግዙ – በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ”  በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ይካሄዳል፡፡

ሁነቱ በኩባንያዎቹ መካከል የገበያ ትስስር ለመፍጠር እና የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ተመላክቷል፡፡

በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ምርቶች፣ አገልግሎቶች እና ግብዓቶችን በማስተዋወቅ ለሀገሪቱ ልማት፣ ለሥራ ፈጠራ እና ለንግድ ሥራ መስፋፋት የሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች እንደሚቀርቡም ነው የተገለጸው፡፡

13ኛውን የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ያዘጋጁት የኢትዮጵያ የንግድ እና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ከኢትዮጵያ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው፡፡

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.