Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች በመዲናዋ 37 ወረዳዎች ዲጂታላይዝ የሲቪል ምዝገባ አገልግሎትን አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ 37 ወረዳዎች ዲጂታላይዝ የሲቪል ምዝገባ አገልግሎትን አስጀምረዋል፡፡

ከንቲባ አዳነች በዛሬው ዕለት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 እና 5 ተገኝተው የአገልግሎት አሰጣጡን መመለከታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

በጉብኝታቸውም ÷በማዕከሎቹ የቴክኖሎጂ ስራዎች፣ የአገልግሎት አከባቢን ምቹ የማድረግ፣ የነዋሪ መረጃ አያያዝ ስርዓት በቴክኖሎጂ በመደገፍ የማደራጀት እንዲሁም ሌሎች አገልግሎትን የሚያቀላጥፉ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡

የዲጂታል አገልግሎት ከተጀመረባቸው የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ የመሬት፣ የገቢዎች፣ የግንባታ ፍቃድ፣ የንግድና የጤና ዘርፎች ላይ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም የመዲናዋን ነዋሪዎች የሚመጥን ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት ለመስጠት የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.