Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ6 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት ከ6 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ የገቢ ግብር መሰብሰቡን የሶማሌ ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ አህመድ መሀመድ እንደገለጹት÷ በክልሉ ከሚገኙ 95 ወረዳዎችና ስድስት የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በቢሮ ደረጃ የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው በ1 ቢሊየን ብር ያህል ብልጫ አለው።

እንደ ምክትል ኃላፊው ገለጻ÷ የተሻለ ገቢ ሊሰበሰብ የቻለው ቢሮው የገቢ አሰባሰብ አሰራሩን በማዘመኑና ህብረተሰቡ የግብር መክፈል ግዴታውን በአግባቡ በመወጣቱ ነው፡፡

የክልሉን ገቢ ለማሳደግ ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካትም በክልሉ ህብረተሰብ ዋና የኢኮኖሚ ምንጮች ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ቢሮው በበጀት አመቱ ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ስራ መግባቱ የተገለፀ ሲሆን÷ ከእቅድ በላይ ለማሳካትም እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.