የሀገር ውስጥ ዜና

የሀረሪ ክልል ካቢኔ ከሸዋል ኢድ በዓል ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ገመገመ

By Feven Bishaw

April 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀረሪ ክልል ካቢኔ ከሸዋል ኢድ በዓል ዝግጅቶችና ከበዓሉ ጋር በተያያዘ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ገምግሟል።

በዚህም በእለቱ የሚመረቁ ፕሮጀክቶችን፣ የክልሉን የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎችን፣ የጽዳትና ውበት ስራዎችንና የአገልግሎት መስጫ ማእከላት ሁኔታን ምልከታ በማድረግ አፈፃፀማቸው ተገምግሞ አቅጣጫ ተቀምጧል ነው የተባለው።

በተደረገው የመስክ ግምገማም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪን ጨምሮ የክልሉ የካቢኔ አባላት መገኘታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በክልሉ ከቀናት በኋላ የሸዋል ኢድ በዓል በድምቀት ይከበራል፡፡