አቶ ደመቀ መኮንን ቡሩንዲ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን ቡሩንዲ ገብተዋል፡፡
አቶ ደመቀ በአራት የአፍሪካ ሃገራት ጉብኝት የሚያደርጉ ሲሆን÷ በታንዛኒያ እና ኮሞሮስ ቆይታ አድርገዋል፡፡
ቡሩንዲ ሶስተኛ የጉብኝታቸው መዳረሻ ሃገር ስትሆን ምሽቱን ቡጁምቡራ ገብተዋል፡፡
በስፍራው ሲደርሱም የሃገሪቱ መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አቶ ደመቀ በቆይታቸው ከሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ኤቭርስቴ ኒዲሽሚዬ ጋር በሁለትዮሽ እና በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከውጭ ጉዳይ ማኒስቴር ቃል አቀባይ ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡