Fana: At a Speed of Life!

የአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ የአስከሬን ሽኝት መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ አስከሬን ቡራዩ ከሚገኘው የአርቲስቱ መኖሪያ ቤት ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አሸኛኘት እየተደረገለት ነው፡፡
 
በአሸኛኘት መርሐ ግብሩ የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ማርች ባንድ፣ የአርቲስቱ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች እንዲሁም የክልሉ እና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
 
የአርቲስት ዘሪሁን የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የተለያዩ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት የሚፈፀም መሆኑ ተገልጿል፡፡
 
አርቲስት ዘሪሁን ወዳጆ በባጋጠመው ህመም ምክንያት በህንድ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቶ ከቀናት በፊት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡
 
አርቲስቱ በኦሮምኛ ቋንቋ በርካታ ሥራዎችን ለሕዝብ በማድረስ አድናቆትና ተወዳጅነትን አትርፏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.