Fana: At a Speed of Life!

ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023 ፎረም ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፍ የንግድ ተቋማትና ባለሃብቶች የሚሳተፉበት “ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023 ” ፎረም መካሄድ ጀምሯል።

በፎረሙ መክፈቻ ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨሰትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ፣ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ፣ ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች ፣ ዲፕሎማቶች፣ የልማት አጋሮችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ለሦስት ቀናት የሚቆየው ፎረም “በኢትዮጵያ ኢንቨስት በማድረግ በልፅጉ – ማራኪ የኢንቨስትመንት አማራጮች ያሏት ምድር” በሚል መሪ ሃሳብ ይካሄዳል፡፡

ከመላው ዓለም የተወጣጡ ከ600 በላይ የንግድ ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሃብቶች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ፎረሙ በኢትዮጵያ ያሉትንና ያልተነኩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ለዓለም ለማስተዋወቅ ምቹ አጋጣሚ እንደሚፈጥር መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።

መርሐ-ግብሩን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ኢትዮ ቴሌኮም ዋና አጋር በመሆን እንዳዘጋጁት የተገለጸ ሲሆን ፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበኩሉ የፎረሙ ሕጋዊ የጉዞ አጋር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከ600 በላይ አዳዲስ የውጭ ቀጥተኛ ባለሀብቶች እንደሚሳተፉበት በተገለጸው ፎረም በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ሦስት ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ ፈሰስ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.