Fana: At a Speed of Life!

አቶ ኡስማን ሱሩር ግብርናን በማዘመን ሀገራዊ ብልጽግናን ማፋጠን እንደሚገባ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርናን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር ሀገራዊ ብልጽግናን ማፋጠን ይጠበቃል ሲሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር ገለጹ፡፡

በደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማስጀመሪያ መድረክ ተካሂዷል፡፡

አቶ ኡስማን በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ምዕራፍ ሁለት በ498 ቀበሌዎች ላይ እየተተገበረ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዘመናዊ የፍራፍሬ፣ የቡና እና የማሕበረሰብ ችግኝ ጣቢያዎችን በማጠናከር በሚሊየን የሚቆጠሩ የቡናና የፍራፍሬ ችግኝ በማዘጋጀትና በማሰራጨት አርሶ አደሩን ቀጥታ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

አዲሱ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በክልሉ የምግብ ሥርዓትን በሚገባ ለማጠናከር የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት እንደሚረዳም ነው ያመላከቱት፡፡

በጌትነት ጃርሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.