Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቡሩንዲ ፕሬዚዳንት ኤቭርስቴ ኒዲሽሚዬ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮቸ ላይ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ትናንት ምሽት ቡሩንዲ መግባታቸው ይታወሳል፡፡

አቶ ደመቀ ለፕሬዚዳንቱ እንደተናገሩት ፥ የኢትዮጵያ መንግስት በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የተፈጠረውን መረጋጋት እና የሀገሪቱን ሰላምና ደህንነት ለማጠናከር ቁርጠኛ ነው።

የዓባይ ተፋሰስ አባል ሀገራት መደበኛው የምክክር ሂደት እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል። ፡፡

አክለውም ኢትዮጵያ ከሱዳን ህዝብ ጎን ሆና እንደምትቀጥልም ነው ያረጋገጡት፡፡

ፕሬዚዳንት ኤቨረስት በበኩላቸው ፥ የኢትዮጵያ እና የብሩንዲ ዘርፈ ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው ታሪካዊ በመሆኑ የበለጠ መሻሻል እንዳለበት ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ሰላም ለአፍሪካ ሰላም ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፥ ኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ከኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ ልምድ እንዲወስዱም መክረዋል፡፡

ብሩንዲ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት በአፍሪካ ህብረት ጥላ ስር የሚደረገውን የሦስትዮሽ ድርድር ትደግፋለችም ነው ያሉት።

በዓባይ ተፋሰስ ሀገራት መካከል የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትም ውይይት ያለውን ጠቀሜታ አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሌሎች ሀገራት ላይ ጉልህ ጉዳት ሳታደርስ የህዝቦቿን ህይወት የማልማትና የመለወጥ መብት እንዳላትም ነው ፕሬዚዳንቱ የተናገሩት።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መልዕክትን ለፕሬዚዳንቱ ሰጥተዋል፡፡

ቀደም ሲል አቶ ደመቀ ታንዛኒያ እና ኮሞሮስን የጎበኙ ሲሆን ፥ ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ከሀገራቱ ጋር የሁለትዮሽ ትብብር ለማድረግ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.