በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 41 ሺህ አልፏል
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ41 ሺህ አልፏል።
በአሜሪካ 759 ሺህ 766 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፥ 41 ሺህ 114 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።
በኒውዮርክ 242 ሺህ 786 ሰዎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው 14 ሺህ 451 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል ነው የተባለው።
በበርካታ ግዛቶች ውስጥም “ቤት ውስጥ ይቆዩ” የሚለውን የመንግስት ትዕዛዝ በመቃወም ዜጎች ሰልፍ እየወጡ ነው ተብሏል።
እንደ ጆን ሆፕኪንስ መረጃ በአሜሪካ በአጠቃላይ 70 ሺህ 980 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገም ችለዋል።
አሁን ላይ በዓለም ከ2 ነጥብ 4 ሚሊየን በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፤ ከዚህ ውስጥ 165 ሺህ 273 ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።
628 ሺህ 816 ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።