Fana: At a Speed of Life!

ፍርድ ቤቱ የእነ ሲሳይ አውግቸውን (ረ/ፕ) መዝገብ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ  

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18 2015 (ኤፍ ) ፍርድ ቤቱ ሕገ መግስቱን በኃይል ለማፍረስ ሲንቀሳቀሱ ነበር ተብለው የተጠረጠሩት የእነ ሲሳይ አውግቸውን (/) መዝገብ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ሲሳይን (/) ጨምሮ 5 ተጠርጣሪዎች ላይ የሰራውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ለሚያዝያ 20 ቀን 2015 . ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

 መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው 8 ቀን ውስጥ በተጠርጣሪዎቹ እነ ሲሳይ አውግቸው (/) ማዕረጉ ቢያበይን (ፕሮፌሰር) አማሃ ዳኘው፣ ሰለሞን ልመንህ እና ሄኖክ አዲስን በሚመለከት የሰራውን የምርመራ ስራ በዝርዝር ለጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ አቅርቧል።

 ተጠርጣሪቹ ሕገ መንግስቱን በኃይል ለመናድ በማሰብ በአማራ ክልል ሁከት፣ ብጥብጥ እና አመጽ በማስነሳት በንብረትና በሰው ላይ በደረሰ ጉዳት ተሳትፎ እንዳላቸው የሚገልፅ በጥናት የተዘጋጀ የሠነድ ማስረጃ ማግኘቱን ፖሊስ አብራርቷል።

 ለበጎ አድራጎት ዕርዳታ በሚል ሰበብ በግልፅ አባላት ተመልምሎ አጣዬ አካባቢ ስልጠና ሲሰጡ እንደነበር የተገኘው ማስረጃ ያሳያል ሲልም ነው ያስረዳው ፖሊስ፡፡

 የገንዘብ ዝውውሮችን ለማጣራትም ለባንኮች ደብዳቤ መጠየቁን እና በተጠርጣሪዎች እጅ የተገኘ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችን፣  የተያዙ የጦር መሳሪያዎችን እንዲሁም በሰለሞን ልመንህ እጅ የተገኙ ሠነዶችን ሕጋዊነት የማጣራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ገልጿል።

 ቀሪ የምርመራ ሥራዎችን አከናውኖ ለማቅረብ 14 ቀን እንዲሰጠውም ነው መርማሪ ፖሊስ የጠየቀው፡፡

 የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ለፖሊስ ከዚህ በፊት የተሰጠው ጊዜ በቂ መሆኑን ጠቅሰው ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ሊሰጥ አይገባም ሲሉ  ተከራክረዋል።

የተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድም ጠይቀዋል።

መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ቢወጡ  ማስረጃ ሊያሸሹብኝ ይችላሉ ሲል ስጋቱን ገልጾ÷ የዋስትና ጥያቄያቸውን ተቃውሞ ተከራክሯል።

 የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ የምርመራ መዝገቡን ተመልክቶ ብይን ለመስጠት ለሚያዝያ 20 ቀን 2015 . ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

 በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.