Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ኡጋንዳ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለስራ ጉብኝት ኡጋንዳ ገብተዋል፡፡

አቶ ደመቀ ኡጋንዳ ሲደርሱ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሄነሪ ኦኬሎ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአራት የአፍሪካ ሀገራት ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት አቶ ደመቀ÷ በዛሬው ዕለት በኡጋንዳ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኡጋንዳ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በኡጋንዳ እየተካሄደ በሚገኘው የሶማሊያ ሰላም ማስከበር ተልዕኮ ሰራዊት ያበረከቱ ሀገራት ጉባኤ ላይ እንደሚሳተፉም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.