በሱዳን ያለውን ግጭት በመሸሽ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱዳን ያለውን ግጭት በመሸሽ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ዮሐንስ ከተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው።
ግጭቱን ሸሽተው በኢትዮጵያ ለተጠለሉ ሰዎችም በመተማ ዮሐንስ ከተማ ተገቢው እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡
የምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ እንደሚያመላክተው እስካሁን የሱዳንን ጨምሮ የ23 ሀገራት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡
ሕጻናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች እንደሚገኙበትም ነው የተገለጸው፡፡
ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ያሉ ሰዎችም በፍላጎታቸው መሰረት ከመተማ ዮሐንስ ወደ ጎንደር እና ሌሎች አካባቢዎች እየተጓጓዙ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር፣ የዞን ከፍተኛ አመራሮች፣ የሚመለከታቸው ጸጥታ አካላትም ሰዎቹ ያለምንም እንግልት ወደ ሚፈልጉት አካባቢ እንዲደርሱ ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው ተብሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!