Fana: At a Speed of Life!

የሸዋል ዒድ ሰላምን አብሮነትን እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎልብት መልኩ ይከበራል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሸዋል ዒድ ክብረ በዓል ሰላምን አብሮነትን እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያጎልብት መልኩ እንደሚከበር የሀረሪ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን የሸዋል ዒድ በዓልን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት÷ የዘንድሮው የሸዋል ዒድ በዓል በክልሉ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በሚያሳይ መልኩ እና የክልሉን ልማትና ዕድገት ለማነቃቃት በሚያስችል ሁኔታ ይከበራል ብለዋል፡፡

ይህ ባህላዊ በዓል በክልሉ የመቻቻል፣ የአብሮነት እና የሰላም ዕሴትን እንዲሁም በተለይ የቱሪዝም ዘርፉን ከማጎልበት አንፃር ጠቀሜታው የጎላ መሆኑንም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት፡፡

የሸዋል ዒድ በዓል አከባበርን በዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

የዘንድሮውን የሸዋል ዒድ በዓል በተሳካ ሁኔታ ለማክበር አስፈላጊውን ዝግጅት ተጠናቋል ነው ያሉትር ርዕሠ መስተዳድሩ።

በሐረሪ ክልል በልዩ ሁኔታ የሚከበረው የሸዋል ዒድ በዓል የሐረርን ታሪክ፣ ዕሴት እና ባህልን ሊያስተዋውቁና ሊገልጹ የሚችሉ ዝግጅቶችን በወንድማማችነት መንፈስ ለታዳሚው ለማቅረብ ዝግጅት መደረጉንም አመላክተዋል፡፡

“ሸዋሊድ ለሰላም፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነት እና ለቱሪዝም ዕድገት” በሚል መሪ ሐሳብ ከነገ ጀምሮ የሚከበረው የሸዋል ዒድ በዓል አብሮነት፣ ፍቅር፣ ሰላም እና ወንድማማችነት የሚጠናከርበት እንዲሆን ተመኝተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.