ስፓርት

ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

By Mikias Ayele

April 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ21ኛ ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ፡፡

9፡00 ላይ አርባምንጭ ከተማን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ በእስማኤል ኦሮ አጉሮ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎ ፈረሰኞቹ ከተከታያቸው ባሕርዳር ከተማ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሥድስት ማስፋት ችለዋል፡፡

በሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር 12፡00 ላይ ሐዋሳ ከተማን የገጠመው ፋሲል ከነማ ሞሐመድ ሞንታ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠራት ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም አፄዎቹ ነጥባቸውን 30 በማድረስ ከሀድያ ሆሳዕና ጋር 5ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የሊጉ 21ኛ ሣምንት ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ነገ ኢትዮ ኤሌክተሪክ ከወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ከመቻል ይገናኛሉ፡፡