የሀገር ውስጥ ዜና

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከጀርመኑ ዓለም አቀፍ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

April 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራና ክህሎት ሚንስትር ሙፈሪሃት ካሚል ከጀርመኑ ዓለም አቀፍ ድርጅት (ኬ ኤፍ ደብሊው)የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ÷ በድርጅቱ ድጋፍና የቅርብ ትትል የተከናወኑ ተግባራት እና የተደረጉ ድጋፎች ውጤታማ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በቀጣይ በድርጅቱ በኩል ተጨማሪ ድጋፍ በሚደረግበትና ግንኙነቱ ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡