ዓለምአቀፋዊ ዜና

ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

April 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂን ፒንግ ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱ ሀገራት መሪዎች ውይይት የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የተደረገ የመጀመሪያ ውይይት መሆኑ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳት ሺ ÷በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ልዑክ ወደ ኬቭ ለመላክ ማቀዳቸውን ገልፀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በበኩላቸው ÷ ቻይና በኬቭ ዲፕሎማቶችን ለመላክ ማቀዷ የሁለቱን ሀገራት ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የሚያጠናክር መሆኑን በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ውይይቱ በፕሬዚዳንት ዘለንስ ግብዣ የተደረገ ሲሆን ፥ የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት መፍትሄ እንዲያገኝ ቻይና ሚናዋን እንደምትወጣ አስታውቃለች፡፡

እየተካሄደ ባለው የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት ቻይና ገለልተኛ አቋም እንዳላትና ጦርነቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ስትገልፅ መቆየቷን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡