የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከእንግሊዙ የማዕድን ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኬፊ ከተሰኘው የእንግሊዝ ወርቅ እና መዳብ አምራች ኩባንያ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
ኬፊ የወርቅ እና መዳብ አምራች ኩባንያ ሲሆን ÷320 ሚሊየን ዶላር የማዕድን ልማት ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ ነው ከኮሚሽኑ ጋር የተፈራረመው፡፡
ከኩባንያው በተጨማሪም ከተለያዩ የገንዘብ ድጋፍ ሰጭ ተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
ስምምነቱ “ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023” የኢንቨስትመንት ፎረም ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የተካሄ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡