ኤምባሲው 60 ተጋላጭ ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መለሰ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጅቡቲ ከሚገኘው ዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባባር 60 ፍልሰተኞችን ወደ ሀገራቸው መመለሱን አስታወቀ፡፡
ከፍልሰተኞቹ መካከል 14 ያህሉ በየመን በአስከፊ ችግር ውስጥ ቆይተው ወደ ጅቡቲ የገቡ መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡
ቀሪዎቹ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመሻገር ጅቡቲ ከገቡ በኋላ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ተገንዝበው ሐሳባቸውን የቀየሩ መሆናቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወጣቶች በሕገ ወጥ ደላሎች በመታለል በዚህ አደገኛ የጉዞ መስመር ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ኤምባሲው አሳስቧል፡፡