Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱ አፈፃፀምና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረቱ ይደነቃል- አምባሳደር ክሪስቶፍ ሬዝላፍ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱን አፈፃፀምና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረቱን የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ክርስቶፍ ሬዝላፍ አደነቁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር አምባሳደር ክርስቶፍ ሬዝላፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው ላይ እንደተገለጸውም÷ የጀርመኑ ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ በቅርቡ በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡

የጀርመኑ ቻንስለር በኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉብኝትም በሀገራቱ መካከል ያለውን ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የበለጠ እንደሚያጠናክረው አምባሳደር ምስጋኑ ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የሰለም ስምምነቱ በጥሩ ሁኔታ እየተፈፀመ መሆኑን አስገንዝበው÷ መንግሥት የተረጋጋ የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር በትጋት እየሠራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በሱዳን የተከሰተው ግጭት በውይይት እንዲፈታም የኢትዮጵያ ፍላጎት ነው ማለታቸውን የውጭ ጉይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የሱዳንን ግጭት ለመፍታት የአፍሪካ ሕብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የሚያደርጉትን  ጥረት  ኢትዮጵያ ታበረታታለች ነው ያሉት፡፡

አምባሳደር ክሪስቶፍ ሬዝላፍ በበኩላቸው÷ የሰላም ስምምነቱን አፈፃፀምና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረቱን አድንቀዋል፡፡

በሌላ በኩል  አሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የውጭ እርዳታ ቢሮ ዳይሬክተር ዳፍና ራንድ  የገንዘብ ሚኒስቴርን ጎብኝተዋል፡፡

ዳይሬክተሯ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኑ ብሊንከን በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱ ሀገራት ትብብር ምልክት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታዋ ሰመሪታ ሰዋሰው በበኩላቸው ÷የአሜሪካ መንግስት  መሰረታዊ አገልግሎቶችን በማቅረብ ረገድ ላደረገው ያልተቋረጠ ድጋፍ  ምስጋና ማቅረባቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.