Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ በሱዳን የነበሩ ዜጎቿ በኢትዮጵያ ድንበር በኩል እንዲወጡ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቀረበች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቱርክ በሱዳን የነበሩ ዜጎቿ በኢትዮጵያ ድንበር በኩል በሰላም እንዲወጡ የኢትዮጵያ መንግስት እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርባለች፡፡

በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሰደር አደም መሃመድ በሱዳን የነበሩ የቱርክ ዜጎችን ለማስወጣት ከተሰየመው የቱርክ ኮሚቴ ዋና ዳይሬክተር ኤሊፍ ኮሞግሉ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኤሊፍ ኮሞግሉ÷ የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳን የሚገኙ የቱርክ ዜጎችን በኢትዮጵያ ድንበር በኩል በሰላም እንዲወጡ እያደረገ ላለው ትብብር እና ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ሃላፊዎቹ ቱርክ እና ኢትዮጵያ የጋራ ጥቅማቸውን ባከበረ መልኩ ያላቸውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ በቅንጅት እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.