የሀገር ውስጥ ዜና

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኑ

By Amele Demsew

April 27, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ፡፡

በዛምቢያ ሉሳካ ሲካሄድ የቆየው የኮንፌዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በካውንስሉ በሙሉ ድምፅ መመረጣቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

#Ethiopia ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!