Fana: At a Speed of Life!

አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በአቶ ግርማ የሺጥላ ግድያ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔ አገኘሁ ተሻገር በአማራ ክልል ብልጽግና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት ግርማ የሺጥላ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል፡፡

የሀሳብ ልዕልና በጠመንጃ በአፈሙዝ የማይገታ ማዕበል መሆኑን ያልተረዱና አርቆ መሳብ የተሳናቸው አካላት በሰለጠነ መንገድ የፖለቲካ ልዩነትን ለማጥበብ በሚደረገው ጥረት እንቅፋት ለመሆን የመረጡት የኪሳራ መንገድ ዛሬም ከጎናችን አንድ ደፋር ጀግና ታጋይ በሚያስቆጭ ሁኔታ እንድናጣ አድርገዋል ብለዋል፡፡

‘’የብልጽግና ጉዟችን ተስፋ በቆረጡ ፅነፈኛ ሃይሎች ሽብር አይደናቀፍም፤  የጓዶቻችን አደራ  በየትኛውም በማንኛውም ሁኔታ እናሳካለን፤ የፅንፈኞች የሽብር ዓላማ በፍፁም አይሳካም ሲሉም ገልጸዋል።

በኪሳራ መንገድ የአመለካከት ልዩነቶችን መፍታትን መሞከር በህዝቦች ላይ መከራን ከመጫን ያለፈ ትርጉም እንደማይኖረውም አንስተዋል፡፡

በዚህ በሠለጠነ ዘመን የዚህ አስተሳሰብ ተሸካሚ ግለሰቦችን ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊታገሉት ይገባልም ነው ያሉት።

አፈ ጉባኤው ጽንፈኝነትን ታግለን የህግ የበላይነት እንዲከበር መስራት አለብን ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡

ለአማራ ክልል ህዝብ፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን፣ ለሟች ቤተሰቦችና  ወዳጅ ዘመዶቻቸውም መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.