የሀገር ውስጥ ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ማገዝ እንደሚገባ አስታወቁ

By Tibebu Kebede

April 20, 2020

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 12 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ማገዝ እንደሚገባ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ የመስጠት መንፈስን እና ማኅበረሰብ መገንባትን ማጠናከር እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ትናንት ዓመት በዓሉን ለታሪክ በሚመዘገብ ሁኔታ ማሳለፍ መቻሉንም አንስተዋል።

እንዲህ ዓይነት በዓላትን የሚያደምቁ የልግስና እና የርኅራኄ ዕሴቶች አብረው ይኖራሉም ነው ያሉት።