Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል ካላቸው ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር በላይ የኢንቨስትመንት ካፒታል ካላቸው አምስት የተለያዩ አገራት ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሌሊሴ ነሜ እና የኩባንያዎቹ ኃላፊዎች ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን ከፈረሙት ውስጥ በሲሚንቶና ሌሎች ዘርፎች ላይ የሚሰማራውና 500 ሚሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያለው ሲኖማ የተሰኘው ኩባንያ አንዱ ነው።

በተጨማሪም በምግብ ማቀነባበሪያና ሌሎች ዘርፎች የሚሰማራውና 45 ሚሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ያለው ኤ አይ ፉድ ኤንድ ዩኒሊቨር ማኑፍክቸሪንግ ሌላኛው ኩባንያ ነው።

በተመሳሳይ በእንጨት፣ ሎጅስቲክስና ሌሎች ዘርፎች 1 ቢሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል ስምምነት ያደረገው ሻንጉ ቲምበር ኤንድ ውድ አሶሲየሽን ኩባንያ መሆኑ መገለፁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ኢትዮ ቺክን ኤንድ ኤጂ ፒ በ30 ሚሊየን ዶላር እንዲሁም ቲያሸ በ80 ሚሊየን ዶላር የኢንቨስትመንት ካፒታል መዋእለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ከኮሚሽኑ ጋረ ተፈራርመዋል።

የተደረጉ ስምምነቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ የሚኖረው ሲሆን÷ ባለሀብቶች ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም ተገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.