የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ በቻይና-አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ትብብር መድረክ ላይ እየተሳተፈች ነው

By Mikias Ayele

April 28, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና-አፍሪካ ዓለም አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ እድገትና ትብብር መድረክ በቻይና ጂናን ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

መድረኩ ቻይና በዘርፉ ያላትን የላቀ ተሞክሮ ለአፍሪካ ሀገራት የምታጋራበትና በትብብር ማዕቀፉ ውስጥ ተጨባጭ የዘርፉን ተግዳሮቶች ለመፍታትና እድገት ለማምጣት በጋራ የሚሰራበት  ነው ተብሏል፡፡

በመድረኩ እየተሳተፉ የሚገኙት  የሥራና ክህሎት  ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ÷ መድረኩ የቻይና እና አፍሪካ እንዲሁም የቻይና እና የኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ትብብር ቴክኖሎጂን ለማሳደግ ሚና አለው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን አቅምና ተሞክሮ በትብብር ለማሳደግ እንደምትጠቀምበት የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው ÷ የቻይና ልምድ ዘርፉን ለማገዝ የማይተካ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

አቶ ተሻለ በሬቻ እና ልዑካቸው ከመድረኩ ጎን ለጎን ከሻንዶንግ አገር ገዥ ጋር የመከሩ ሲሆን ÷በዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢትዮጵያን የልማት አቅጣጫዎች ተከትሎ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል ፡፡

ከግዛቷ ጋር የተጀመረው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የግዛቷ አመራሮች ድጋፍ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውንም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡