የአቶ ግርማ የሺጥላ የአስከሬን ሽኝት የፊታችን እሑድ በወዳጅነት አዳባባይ ይከናወናል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቶ ግርማ የሺጥላ የአስከሬን ሽኝት እሑድ ሚያዝያ 22 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ወዳጅንት አደባባይ እንደሚከናወን የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው ገለጸ፡፡
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ በወላጆቻቸው ፍላጎት እና ጥያቄ መሰረት በተወለዱበት ሰሜን ሸዋ ዞን መሀል ሜዳ እንደሚፈጸም አሚኮ ዘግቧል፡፡
የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው መግለጫ÷ የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ከፍ ባለ ሁኔታ እንዲፈጸም የተለያዩ ኮሚቴዎች መዋቀራቸው ተገልጿል፡፡
በወዳጅነት አደባባይም÷ የአቶ ግርማ የሺጥላ ባልደረቦች ፣ የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት እሑድ ከ1፡00 ጀምሮ ይከናወናል ነው የተባለው፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!