Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ፋብሪካ ለማቋቋም መግባባት ላይ ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ እና የቻይና ምድር ባቡር ሮሊንግ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶችን ለማምረት የሚያስችል ውይይት አደረጉ፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አውቶቡስ ፋብሪካ ለማቋቋም መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አምባሳደር ሱሌይማን ደደፎ ÷ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች እንዲመረቱ በትኩረት እንሠራለን ብለዋል፡፡

የቻይና ምድር ባቡር ሮሊንግ አክሲዮን ማኅበር ከኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ጋር ለመሥራት ፍላጎት ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

የሁለትዮሽ ውይይቱን ተከትሎ ሁለቱ አካላት በቅርቡ የመግባቢያ ስምምነት ለመፈራረም መግባባት ላይ መድረሳቸውን የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.