Fana: At a Speed of Life!

በዛምቢያ በተካሄዱ የታዳጊዎችና የወጣቶች አትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጀመሪያው ቀን በዛምቢያ ንዶላ በተካሄዱ የታዳጊዎችና የወጣቶች አትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

በዚህም በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች ከ20 ዓመት በታች አስማረች አንለይ 1ኛ ሆና በማጠናቀቋ የወርቅ ሜዳሊያ ስታጠልቅ፣ የኔዋ ንብረት 2ኛ በመሆን ስታጠናቅቅ አይናዲስ መብራቱ በ3ተኝነት ደረጃ አጠናቃለች፡፡

በተጨማሪም ከ18 ዓመት በታች 1500 ሜትር ሴቶች፣ አሰለፍ አማረ 3ኛ ሆና የነሃስ ሜዳልያ ስትሸለም ፥ በዚሁ ርቀት በተመሳሳይ እድሜ በወንዶች ፈይሳ ኢያሱ 6ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.