Fana: At a Speed of Life!

አቶ ግርማ የሺጥላ የኖረው ለህዝብ  ዓላማ ነው -ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ግርማ የሺጥላ የኖረው ለህዝብ ዓላማ ነው ሲሉ የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

ርዕሰ መስተዳር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን ሽኝት ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም÷በተከታታይ በመሪዎች ላይ የሚደረገው ግድያ የአማራን ህዝብ ስቃይና መከራ ለማራዘም በሚሰሩ ፅንፈኛ ሀይሎች ቀጣይነት ያለው መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

“የወንድማችን ግርማ መሥዋዕትነት በተለይ ለአመራራችን የሚያስተላልፈው መልእክት ሁላችንም የያዝነውን ዓላማ ለማሳካት እስከ መሥዋዕትነት ቆርጠን ለመሄድ የግድ የሚለን መሆኑን ነው” ብለዋል።

አቶ ግርማ የሺጥላ ታጋይ፣ ታታሪ እና ቆራጥ እንደነበሩ ጠቅሰው÷የጥቃቱ ዜና ለህዝባችንና ለአመራራችን እጅግ አስደንጋጭ፣ መራር እና ልብ ሰባሪ ሆኗልም ብለዋል፡፡

ሐዘኑ ይበልጥ ተጠናክረን እና አንድነታችንን ጠብቀን ለጋራ ሰላማችን እና ልማታችን እንድንነሣ እንጂ ወደ ኋላ የሚመልሰን አይደለም ነው ያሉት፡፡

በመሆኑም በየአካባቢው ለሰላም እና ለልማት እንደተለመደው አንድነታችንን አጠናክረን ትግላችንን እንቀጥል ሲሉም  ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.