Fana: At a Speed of Life!

የአቶ ግርማ የሺጥላ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቶ ግርማ የሺጥላ የቀብር ሥነ-ሥርዓት በትውልድ ቦታቸው ሰሜን ሸዋ ዞን መሃል ሜዳ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ የአቶ ግርማ የሺጥላ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ባልደረቦች እንዲሁም የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የአቶ ግርማ የሺጥላ አስከሬን ቤተሰቦቻቸው፣ የስራ ባልደረቦች፣ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ ጠዋት በወዳጅነት አደባባይ አሸኛኘት ተደርጎለታል፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በወላጆቻቸው ፍላጎት እና ጥያቄ መሰረት ነው በተወለዱበት ቦታ ሰሜን ሸዋ ዞን መሃል ሜዳ ከተማ የተፈጸመው፡፡

በቀብር ሥነ ሥርዓቱ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አሥተዳደሪ መካሻ ዓለማየሁ÷ግርማ በጣም ደፋር፣ ፊት ለፊት ተናጋሪ ለአመነበት ሀሳብ የማይታጠፍ ጀግና እና የቁርጥ ቀን ልጅ ነበር ብለዋል፡፡

መንግሥትና ሕዝብን በታማኝነት እና በቅንነት አገልግሏል፤ ለእኔ ሳይል ለሕዝብ ሲል ኖሯልም ነው ያሉት፡፡

ሰሜን ሸዋ ላይ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ አስተዋጽዖ አድርጓል ያሉት ዋና አሥተዳዳሪው÷ በዞኑ የተሠሩ ፋብሪካዎች ለእርሱ እንደ ሐውልት ቆመው ምስክር ሆነው ይኖራሉ ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.