Fana: At a Speed of Life!

በበሪሶ አመሎ (ዶ/ር)  የተመራ  ልዑክ የጅቡቲ ዶራሌህ ሁለገብ ወደብን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ የጅቡቲ ዶራሌህ ሁለገብ ወደብን ጎብኝቷል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው እና ልዑካቸው ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍና የነጻ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር አቡበከር ኦማር ሃዲ ጋርም ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ መካከል በባህር እና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ያለውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ጉብኝት የኢትዮጵያና ጅቡቲ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ  ዘርፍን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት መገለጹንም  የኤምባሲው  መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.