Fana: At a Speed of Life!

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎች ዝርዝር ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአማራ ክልል እየወሰደ ባለው እርምጃ በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል በአማራ ክልል እየወሰደ ባለው እርምጃ  ህቡዕ አደረጃጀት ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ የተገኙ 47 ተጠርጣሪዎችን ከበርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ ቦንቦችና ተቀጣጣይ ፈንጂዎች እንዲሁም ከሳተላይት መገናኛ መሣሪያዎች እና የተለያዩ መረጃዎችን ከያዙ ላፕቶፖች ጋር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል።

ግብረ ሃይሉ ÷ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ የእነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የሚዲያና ፕሮፓጋንዳ ክንፍ በመሆን ከሀገር ውስጥ እና ከተለያዩ የውጭ ሀገራት በወንጀል የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚህ መሰረትም

  1. ሀብታሙ አያሌው
  2. ምንአላቸው ስማቸው
  3. ብሩክ ይባስ
  4. እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ
  5. ዘመድኩን በቀለ
  6. ልደቱ አያሌው
  7. መሳይ መኮንን
  8. ጎበዜ ሲሳይ
  9. ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ)
  10. በለጠ ጋሻው እና
  11. ሙሉጌታ አንበርብር ናቸው

እነዚህ ጽንፈኛ ኃይሎች የሀሰት ወሬዎችን በመፍጠር እና ከፍተኛ የሽብር ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ህዝቡን በብሄር እና በሃይማኖት በመከፋፈልና በማጋጨት የክልል እና የፌደራል መንግሥትን በኃይል ለመጣል እንዲሁም ሀገሪቱ ከጀመረችው የለውጥና የልማት መንገድ ወጥታ ወደ ለየለት ሁከትና ትርምስ እንድትገባ በህቡዕ ተደራጅተው እየሠሩ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

በሀገር ውስጥና በውጭ ሆነው በሀሰት ሀገር ለማፍረስ የሚሰሩ እነዚህን ጨምሮ ሌሎችም በህቡዕ አደረጃጀቱ ውስጥ ያሉ ግለሰቦችም ጭምር በሽብርተኝነት ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ተጠቁሟል፡፡

እነዚህ የሽብር ኃይሎች ከሚኖሩባቸው ሀገራት በአለም አቀፍ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) እንዲሁም እነሱ ከሚኖሩባቸው ሀገራት መንግሥት የፀጥታ እና የደኅንነት ተቋማት ጋር በተመሠረቱ የትብብር ማዕቀፎች አማካኝነት ወደ ሀገር ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ በህግም እንዲጠየቁ እየሰራ መሆኑን እና ይህንኑ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

እነዚህ ውጭ ሀገር የሚኖሩ ተፈላጊዎች ከውጭ ሀገር በሚያገኙት እና በሀገር ውስጥ ያላቸውን ሀብት ተጠቅመው ለዚህ እኩይ ተግባር እያዋሉ መሆኑን በምርመራ የተደረሰበት ስለሆነ በሀገር ውስጥ ያላቸውን ሀብት የመለየት እና በህግ የመቆጣጠር ስራ እየተሰራ መሆኑንም ነው ግብረ ሃይሉ ያስታወቀው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.