Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለኑሮ ወደ አሜሪካ የሚደረግ ጉዞን ሊያግዱ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት  ዶናልድ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ  ወረርሽኝ ምክንያት ወደ አሜሪካ ለኑሮ በቋሚነት  የሚደረግን ጉዞ ላልተወሰነ ጊዜ እንደሚያግዱ አስታውቀዋል።

ፕሬዜዳንት ትራንፕ ቫይረሱን የማይታየው ጠላት የሚል ስያሜ  የሰጡት ሲሆን÷  እገዳው የአሜሪካውያንን የስራ እድሎች  የሚያስጠብቅ ነውም ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በክልከላው ላይ ዝርዝር መረጃዎችን ከመስጠት ቢቆጠቡም፤ ለስራ  እና የተማሪ ቪዛ ያላቸው ወደ አሜሪካ የሚጓዙ ሰዎች እገዳው አይመለከታቸውም ነው የተባለው።

ከዚያም ባለፈ በዚህ እገዳ የትኞቹ ፕሮግራሞች ሊጎዱ እንደሚችሉ  የተገለጸ ነገር አለመኖሩም ነው የተነገረው።

በሌላም በኩል ተቺዎች  ድርጊቱ የሀገሪቱ መንግስት  ወረርሽኙን እንደምክንያት በመጠቀም ስደተኞች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማድረግ  ያለመ ነው ብለዋል።

በአሜሪካ እስካሁን ድረስ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከ787 ሺህ በላይ የሚሆኑት ሰዎች የተያዙ ሲሆን፥ ከ42 ሺህ የሚበልጡ ደግሞ በበሸታው ምክንያት ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ የሚወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ምንጭ፦ ቢ.ቢ.ሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.