የሀገር ውስጥ ዜና

የሠራተኞችን ጥያቄ ለመመለስ መንግስት ጥረት እያደረገ ነው- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

By ዮሐንስ ደርበው

May 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሠራተኞችን ጥያቄ ደረጃ በደረጃ ለመመለስ መንግስት ከኢትዮጵያ የሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ሚኒስቴሩ ለዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በመልዕክቱም÷ በተለይም ኢትዮጵያን ለማልማት ያላሰለሰ ጥረት ለሚያደርጉ በሁሉም መስክ የተሰማሩ ታታሪ ሠራተኞችን የምናከብርበት እና የምናመሰግንበት ልዩ ቀን ነው ብሏል፡፡

በእስካሁኑ ሂደት የተደረጉ ጥረቶችን የበለጠ ለማጠናከር በየደረጃው አዳጊ ከሆኑ ፍላጎቶች የሚመነጩ የሠራተኛውን ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስ በመንግስት በኩል ልዩ ልዩ ጥረቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም ነው ሚኒስቴሩ የገለጸው፡፡

ለዚህም ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ጋር በቅርበት በመስራት ላይ መሆኑን ጠቁሞ÷ በቀጣይም ይኸው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ነው ያለው፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!