Fana: At a Speed of Life!

በ9 ወራት ከ324 ቢሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታክስ እንዲሁም ከአገር ውስጥና የውጭ ቀረጥ ከ324 ቢሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ “ግብር ለአገር” በሚል መሪ ሐሳብ በአገር አቀፍ ደረጃ ያስጀመረው ከየካቲት እስከ የካቲት ለአንድ ዓመት የሚቆይ የታክስ ንቅናቄ ላይ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የገቢዎች ቢሮ ኃላፊዎች ጋር በአዲስ አበባ እየተወያየ ነው።

የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በውይይቱ ላይ የገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ቀረጥና ታክስ 328 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 324 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

ንቅናቄውን በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ በማድረግ የታክስና ጉምሩክ የሕግ ተገዢነትን ማረጋገጥ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ይህም እንደ አገር የተያዘውን የለውጥ ጉዞ እውን ለማድረግ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.