Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ሚኒስትሮች ልዑክ በአዳአ ወረዳ የስንዴ ልማትን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ሚኒስትሮችና ሌሎች የስራ ኅላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በምስራቅ ሸዋ ዞን አድአ ወረዳ  የስንዴ ልማት ጎብኝቷል።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር  ሽመልስ አብዲሳ  ከኒጀር፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያና ኮትዲቯር ከተውጣጡ የግብርና፣ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት፣ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይና ሌሎች ተቋማትን የወከሉ ሚኒስትሮችና ሌሎች የስራ ኅላፊዎች ጋር በመሆን የስንዴ ልማት  ጎብኝተዋል።

ለልዑካን ቡድኑ በግብርና ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ  ገለጻ ተደርጓል።

ከኒጀር፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያና ኮትዲቩዋር የተውጣጡ የግብርና፣ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት፣ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይና ሌሎች ተቋማትን የወከሉ ሚኒስትሮችና ሌሎች የስራ ኅላፊዎችን ያካተተ  ልዑክ በኢትዮጵያ ለአራት ቀን የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትናንት አዲስ አበባ መግባቱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.