Fana: At a Speed of Life!

በበሪሶ አመሎ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ የታጁራ ወደብና የዳመርጆ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ/ር) የተመራ ልዑካን ቡድን በጅቡቲ የስራ ጉብኝት እያደረገ ነው፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ በጅቡቲ ቆይታው የታጁራ ወደብና የዳመርጆ ኢንዱስትሪያል ፓርክን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
 
በጉብኝት መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ያላቸው ስትራቴጂያዊ አጋርነት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
 
የልዑካን ቡድኑ አባላት በቆይታቸው ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍና የነጻ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር አቡበከር ኦማር ሃዲ ጋር መወያየታቸውንም የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.