የግንባታ ፕሮጀክቶች የስራ ቦታን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል የሚያስችል መመሪያ ሊተገበር ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የግንባታ ፕሮጀክቶች የሥራ ቦታን ከኮሮናቫይረስ ለመከላከል የሚያስችል መመሪያ ሊተገበር መሆኑን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ዛሬ በሰጠው ምግልጫ፥ መመሪያው የኮሮናቫይረስ በግንባታ ቦታዎች ላይ በሚሰሩ ዜጎች ጉዳት እንዳያደርስና የቫይረሱን ስርጭትም አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ነው ብሏል።
በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የተዘጋጀውና የዘርፉ ባለድርሻ አካላትም ጭምር የመከሩበት መመሪያው፥ በግንባታ ዘርፍ የሥራ ቦታዎች ደህንነትን ለማስጠበቅ ትልቅ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል።
በመመሪያው መሰረትም ማንኛውም አሰሪ በሥራ ቦታዎች በሰራተኞች ደህንነት፣ ጤንነት እንዲሁም በሕብረተሰቡ እና በአካባቢው ላይ ጉዳት እንዳያስከትሉ ማድረግ ይኖርብርታል።
በዚህ መሰረትም
1. በየትኛውም የግንባታ ሳይት የሰራተኞችን ደህንነት እና ጤንነት የሚከታተል የጤና ባለሙያ መመደብ
2. በሰራተኞች መግቢያና መውጫ ሰአት በጤና ባለሙያዎች ተደጋጋሚ የግንዛቤ መፍጠር ስራ መስራት
3. ከሰራተኛ ውጭ ወደ ግንባታ ሳይቶች ማንኛውም ሰው እንዳይገባ ማድረገ አስፈላጊ ጉዳይ ካለው እና ፈቃድ ከተሰጠውብቻ ይገባል
4. ሰራተኞች በቀን ቢያንስ ከ3 ጊዜ ያላነሰ የሙቀት ልየታ ማድረግ
5 ለግንባታ ግባት የሚሆኑ ቁሶችን ባግባቡ መጠቀም እና በሚጠቀሙበት ወቅትም በኬሚካል ማጽዳት
6. የግንባታው ሰራተኞች በተቻለ መጠን በግንባታው ተሽከርካሪ እንዲጠቀሙ ማድረግ
7 በግንባታ ቦታዎች ላይ አስፈላጊ የንጽህና መጠበቂያዎች ፥ጓንት እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችንም ማቅረብ እንደሚኖርባቸው በመመሪያት ተቀምጧል።
የመመሪያም ተግባራዊነት የሚከታተል እና የሚቆጣጠር አካል እንዲኖር መደረጉንም ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመላክቷል።
በይስማው አደራው