Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የወጣቶች የሕዳሴ ግድብ ግንባታ የቦንድ ግዢ ንቅናቄ መርሐግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የወጣቶች የቦንድ ግዢ ንቅናቄ መርሐ ግብር ዛሬ በይፋ አስጀምሯል።

የቦንድ ግዢ መርሐግብሩ “እኔም ድርሻ አለኝ” በሚል መሪ ቃል ለሶስትተከታታይ ሳምንት እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በንቅናቄ ማስጀመሪያው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ኃላፊ በላይ ደጀን፣ በአዲስ አበባ የሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ ቤት ኃላፊ ምስክር ነጋሽና የወጣቶች ሊግ ጽ/ ቤት ኃላፊ መለስ አባተ ተገኝተዋል፡፡

በቦንድ ግዢ ንቅናቄው ከመዲናዋ ወጣት ከ80 ሚሊየን ብር በላይ ለማሰባሰብ መታቀዱን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወጣት መለስ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሕዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽ÷ ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ወጣቶቹ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

ወጣቶች ለግድቡ ግንባታ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉም አቶ ምስክር ጥሪ ማቅረባቸውንም ኢዜኤ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.