Fana: At a Speed of Life!

ተመድ የሰላም ስምምነት ትግበራውን እንደሚደግፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ትግበራን በሁሉም መስክ እንደሚደግፍ አስታወቀ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ጉዳይ ሚኒስት ደመቀ መኮንን ከተመድ ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሀመድ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትም አቶ ደመቀ መኮንን የሰላም ሂደቱ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው የሰላም አጀንዳውን በሌሎች አካባቢዎች ለመፈፀም መንግስት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህን ጥረት የሚመጥን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል፡፡

ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ መፍታቷን አድንቀው፥ ፈታኝ የሆነውን የሰላም ሂደት ትግበራ በሁሉም መስክ እንደግፋለን ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመልሶ ማቋቋም ዳግም ግንባታ እቅዱን ማገዝ እንደሚገባ በመጥቀስም፥ ሰላሙ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.