Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ከቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ቡራክ አክሰፐር ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ቱርክ መካከል ባለው የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን ግንኙነት ዙሪያ መክረዋል፡፡
 
በቀጠናዊና ሌሎች መድረኮች ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አምባሳደር ቡራክ ቱርክ በቅርቡ በገጠማት የርዕደ መሬት አደጋ ኢትዮጵያ ላደረገችው ድጋፍ እና ላሳየችው አጋርነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
በሱዳን የነበሩ ዜጎችንም እንዲወጡ በማድረግ ረገድ ኢትዮጵያ ለተጫወተችው በጎ ሚና ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል።
 
ሁለቱ አካላት በሱዳን ያለው ግጭት ረግቦ ሁለቱ ተፋላሚ አካላት ችግሮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ያላቸውን መልካም ምኞትም ገልፀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.