የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን የመለየት ስራ እየተከናወነ ነው 

By Shambel Mihret

May 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ የክልሉን ፀረ ሙስና ኮሚቴ የስራ እንቅስቃሴን ገምግመዋል፡፡

በግምገማው ወቅት ከመቶ በላይ ጥቆማዎች መቅረባቸውን የፀረ ሙስና ኮሚቴው  በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

በቀረቡት ጥቆማዎች መሰረትም በቂ መረጃና ማስረጃ የተገኘባቸው ተጠርጣሪዎች መለየታቸው  ነው የተገለጸው፡፡

በቅርቡም ግለሰቦችን ተጠያቂ ማድረግ እንደሚጀመር ኮሚቴው  መግለጹን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

አቶ ደስታ ኮሚቴው የሄደበት ርቀት ጥሩ መሆኑን ጠቅሰው÷ በክልሉ ሙስናን ለመግታት ኮሚቴው የጀመረውን ስራ በማጠናከር ምርመራውን አጠናቆ ወደ ተግባር እንዲሸጋገር አቅጣጫ አስቀምጠዋል።