Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች የ7 ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች የሰባት ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማርዲያት ከሱዳን ጦር ዋና አዛዥ ጀኔራል አብደል ፈታህ አልቡርሃን እና ከሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሃይሎች ዋና አዛዥ ሞሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ጋር በስልክ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም÷ ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች የሰባት ቀን የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱም ከፊታችን ሐሙስ ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት የሚተገበር መሆኑን የደቡብ ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ዛሬ ባደረገው አስቸኳይ ውይይት÷ በሱዳን የተከሰተው ግጭት በአስቸኳይ መቆም እንዳለበት ማሳሰቡ ይታወሳል።

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች የደረሱትን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲያከብሩና ስምምነታቸውንም ሊያጸኑ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥቷል።

በሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች መካከል በተፈጠረው ግጭት እስካሁን ከ500 በላይ ዜጎች ለህልፈት መዳረጋቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስፍሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.