Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቱርክ ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቱርክ በዲፕሎማሲ፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት መስክ  ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማሳደግ ተስማሙ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ከቱርክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቡራክ አክፓር ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቻውም አምባሳደር ምስጋኑ÷ ስለ ፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ትግበራ ገለፃ ማድረጋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ቱርክ አስፈላጊውን ድጋፍ እንድታደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቡራክ አክፓር በበኩላቸው÷ የመንግስትን የሰላም ጥረት አድንቀው የቱርክ የንግድ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ መሰማራት ይፈልጋል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.