የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ በጅቡቲ የሚገኙ ስደተኞችን ለመመለስ እየተሠራ ነው አሉ

By Alemayehu Geremew

May 03, 2023

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ መንግሥት ጋር በመተባበር በሀገሪቷ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሠሩ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

አምባሳደር ብርሃኑ በ “ነጋድ” የስደተኞች ማቆያ ማዕከል የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን መጎብኘታቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በስደተኞች አያያዝ ላይ ከማዕከሉ አዛዥ ሌ/ኮሎኔል ኦማር ዩሱፍ ጋር መምከራቸውንም ነው ያመላከቱት፡፡