Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡

9፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ መቻል ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ከነዓን ማርክነህ እና እስራኤል እሸቱ የመቻልን ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥሩ÷ ብቸኛዋን ድሬዳዋ ጎል ሙኸዲን ሙሳ አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም መቻል አንድ ደረጃ በማሻሻል 10ኛ ላይ ሲቀመጥ በአንጻሩ ድሬዳዋ አንድ ደረጃ ዝቅ በማለት 11ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

12፡00 ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክን የገጠመው ኢትዮጵያ መድን በተመሳሳይ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

ሀቢብ ከማል እና ብሩክ ሙሉጌታ ጎሎች የመድንን ሁለት ጎሎች ሲስቆጥሩ÷ አብዱራህማን ሙባረክ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ብቸኛ ጎል ባለቀ ደቂቃ አስቆጥሯል፡፡

የውድድር ዓመቱ የዋንጫ ተፎካካሪ መሆን የቻለው መድን ነጥቡን 41 በማድረስ ደረጃውን ማስጠበቅ ችሏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.