Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ መርሐ ግብር መድረክ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የአስተዳደሩ እንዲሁም የፌደራል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በመርሐ ግብሩ ላይም የአምራቾች የምርት አውደ ርዕይ መቅረቡን የአዲስ አበባ የሥራ ኢንተርፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በመካሔድ ላይ ያለውን የኢትዮጵያ ታምርት የንቅናቄ ያዘጋጀው የአዲስ አበባ የሥራ ኢንተር ፕራይዝ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሲሆን÷ መርሐ ግብሩ ለአንድ ቀን እንደሚቆይ ተመላክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.