Fana: At a Speed of Life!

አጃይ ባንጋ አዲሱ የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ባንክ አጃይ ባንጋን አዲሱ ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።

ባንኩ በትውልደ ህንዳዊ በዜግነት ደግሞ አሜሪካዊውን የቀድሞ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመት ባለሙያ በፕሬዚዳንትነት መምረጡን አስታውቋል።

የዓለም ባንክ የቦርድ አመራር አባላት አጃይ ባንጋን በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ በፕሬዚዳንትነት እንዲመረጡ ይሁንታን ሰጥተዋቸዋል።

ይህን ተከትሎም የአሁኑን አሜሪካዊ የባንኩን ፕሬዚዳንት ዴቪድ ማልፓስን በመተካት በመጪው ሰኔ ወር ኃላፊነቱን ይረከባሉ ነው የተባለው።

የአሁኑ የባንኩ ፕሬዚዳንት ማልፓስ ከዓየር ንብረት ለውጥ እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ፈጣን ምላሽ አልሰጡም በሚል ከኃላፊነት እንዲለቁ ግፊቱ መጨመሩን ተከትሎ ከመልቀቂያ ጊዜያቸው ቀደም ብለው ስልጣናቸውን ይለቃሉ ተብሏል።

ተመራጩ ፕሬዚዳንት ከዚህ ቀደም በፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ከባለሙያነት እስከ ከፍተኛ ኃላፊነት የሰሩ መሆናቸውን የባንኩ መረጃ ያመላክታል።

የ63 አመቱ ባንጋ ማስተር ካርድን ለ11 ዓመታት በውጤታማነት መምራታቸው ይነገራል።

አዲሱን ፕሬዚዳንት በተመለከተ የወጣ መረጃም ባንጋ 206 ሚሊየን ዶላር የተጣራ ሃብት እንዳላቸው ያመላክታል።

አጃይ ባንጋ ህንድ ውስጥ በጣም ከሚገለለውና ከሚገፋው ሲኸ ከተባለው ማኅበረሰብ የተገኙ ሲሆን፥ ህንድን ከ15 አመታት በላይ በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ማንሞሃን ሲንግም ከዚህ ማኅበረሰብ የተገኙ ናቸው።

የእርሳቸው ወደ ስልጣን መምጣትም ለህንዳውያን በተለይም ለተገኙበት ማኅበረሰብም ሆነ በየሀገራቱ በተለያዩ ልማዳዊ ሰበብ ለሚገለሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ክብር እና ኩራት እንደሚሆን ይታመናል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.