Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ኢንዱስትሪዎች ዳግም ወደ ስራ እንዲገቡ በቅንጅት እየተሰራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታውቋል፡፡

የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የኢንዳስትሪ ቢሮ ም/ኃላፊ መሃሪ ገብረ-ሚካኤል÷የሰላምስምምነቱን ተከትሎ ጉዳት የደረሰባቸው አምራች ኢንዳስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

አሁን ላይ ለሰራተኞች የሶስት ወር ደመወዝ በመክፈል ወደ ስራ እንዲመለሱ የማሰባሰብ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አምራች ኢንዳስትሪዎችን ወደ ስራ ለመመለስ በተደረገ ጥረት ስራ የጀመሩ እንዳሉ ጠቅሰው÷ በኢንዳስትሪ ፓርኮች ሲያለሙ ለነበሩ የውጭ ባለሃብቶች ወደ ስራ እንዲመለሱም መስራት ይጠይቃል ብለዋል።

በክልሉ የገቢ ምርቶችን በመተካት የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት የሚችሉ ትላልቅ ፍብሪካዎች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የተሟላ ስራ እንዲጀምሩ የሚያስችል ዕቅድ በዝግጅት ላይ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.